የ6ኛ ዕዝ ጠላትን መደምሰስ በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

ሐምሌ 7/2014 (ዋልታ) የ6ኛ ዕዝ የሠራዊት አባላት በቀጠናው ሊቃጣ የሚችለውን ትንኮሳ በመመከት ጠላትን መደምሰስ በሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝ የዕዙ ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ተስፋዬ ወልደማሪያም ገለፁ።

ዕዙ ከዚህ ቀደም ባካሄዳቸው ዘመቻዎች የአሸባሪውን የሕወሓት ከገባበት ቦታ ጠራርጎ በማስወጣትና ቅስሙን በመስበር በጠላት ላይ ከፍተኛ የሆነ የስነ-ልቦና ውድቀት እና ኪሳራን በማድረስ ውጤታማ ግዳጆችን የፈፀመ እና በርካታ ጀግኖችን ያፈራ ዕዝ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም የመከላከል ቁመናን በመያዝ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመውሰድ ዕዙ የተሻለ አቅም እንደፈጠረ እና የትኛውንም ዓይነት ግዳጅ መፈፀም በሚያስችል አስተማማኝ ቁመና ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያሳያል።