የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ

ሐምሌ 1/2014 (ዋልታ) በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሲሰጥ የነበረው የ2014 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በፈተና አሰጣጥ ሂደት ላይም ምንም አይነት ችግር እንዳላጋጠመ የሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አመለወርቅ ህዝቅኤል ገልፀዋል።

ተማሪዎችም ፈተናውን በጨዋነት እና እርጋታ እንደወሰዱም ተናግረዋል።

የክልል እና ከተማ አስተዳደር ቢሮዎችም ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን ለተወጡ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

በቀጣይም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 27/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳል።