ዩኒቨርሲቲው ከአንድ ሺህ በላይ ተማሪዎችን በነገው እለት ያስመርቃል

ሰኔ 25/2013 (ዋልታ) – የጅንካ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 1ሺህ 11 ተማሪዎች ለሁለተኛ ዙር በነገው እለት ያስመርቃል።

በ2010 ዓ.ም ከተመሰረቱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው የጅንካ ዩኒቨርሲቲ በአጭር ጊዜ የተሰጡትን ተልዕኮዎች በብቃት እየተወጣ ይገኛል።

(በጌታቸው መኮንን)