ዩኒቨርሲቲው የኤፍ ኤም ሬዲዮ አገልግሎት ጀመረ

ግንቦት 25/2014 (ዋልታ) የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባው የማኅበረሰብ ተኮር ኤፍ ኤም 104.5 ሬድዮ ጣቢያ ዛሬ ተመርቆ የሙከራ ስርጭቱን ጀመረ።

ዩኒቨርሲቲው ያስገነባው ማኅበረሰብ ዐቀፍ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያውን መርቀው የከፈቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዑባህ አደም ናቸው።

ከንቲባ ከድር የጣቢያው አገልግሎት መጀመር በፈጣንና በትክክለኛ መረጃ  የታገዘ ማኅበረሰብ በመፍጠር ለተጀመረው ልማት እና ሰላም ዳር መድረስ ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል ብለዋል።

የማኅበረሰብ ሬድዮው ድሬዳዋን የምስራቅ ኢትዮጵያ የንግድ እና የኢንዱስትሪ ከተማ የማድረጉን ጉዞ ለማሳካት ወሳኝ አበርክቶ እንደሚኖረው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡