ዩክሬን የመጀመሪያውን ኤፍ-16 ተዋጊ ጀት ተረከበች



ሐምሌ 28/2016 (አዲስ ዋልታ) ዩክሬን የመጀመሪያውን የኤፍ-16 ተዋጊ ጀል ከአሜሪካ መቀበሏን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ አስታወቁ፡፡

ፕሬዝዳቱ የመጀመሪያውን ተዋጊ ጀት መረከባቸውን ሲገልጹ “ኤፍ – 16 ጀቱ ዩክሬን ገብቷል፡፡ አሳክተነዋል” ብለዋል፡፡

ዘለንስኪ ጀቱ አገራቸው ከ18 ወራት መጓተት በኋላ እንድትረከብ ላገዟት ዴንማርክ፣ ኔዘርላንድስንና አሜሪካን አመስግነው ተጨማሪ ተዋጊ ጀት እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል፡፡

አዲስ የተረከቡት ኤፍ – 16 በሩሲያ ሰራሽ አሮጌ ጀቶች የሚዋጋውን የዩክሬንን አየር ኃይል እንደሚያጠናክረው ለጦርነቱ አዲስ ምዕራፍ መሆኑን ቢቢሲ ዘገቧል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የጦር ዕርደታ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹ 2023 ድረስ 65 ኤፍ – 16 ተዋጊ ጀቶች ለመስጠት ቃል መግባታቸው ይታወሳል፡፡

ኤፍ – 16 ለመጀመሪያ ጊዜ መመረት የጀመረው እ.ኤ.አ በ1978 ሲሆን በአሁኑ ወቅት በርካታ የአውሮፓ አገራት ጀቱን አሜሪካ በ2015በ ማምረት በጀመረችው ኤፍ – 35 በመተካት ላይ ናቸው፡፡