ያለን ሃብታችን መቶ ሚሊየን ህዝብ መሆኑን አውቀን ኢትዮጵያችንን ለመቀየር በጋራ እንቁም- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

ግንቦት 17/2013 (ዋልታ) – ያለን ሃብታችን መቶ ሚሊየን ህዝብ መሆኑን አውቀን ኢትዮጵያችንን ለመቀየር በጋራ እንቁም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው “ኢትዮጵያዊያን ብዙ ያለን፤ ያንንም የማናውቅ፤ ማጠንከር የሚገባንን፣ ጠንካራ ጎናችንን የዘነጋን እና የሌለንን በማለም የቆየን ነን” ብለዋል።

ያለን ሃብታችን መቶ ሚሊየን ህዝብ መሆኑን አውቀን፤ ተከባብረን፣ ተፈቃቅረን፣ ተደምረን ኢትዮጵያችንን ለመቀየር በጋራ እንቁም ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡