ያማረ ቢሮ ብቻ ሳይሆን ያማረች አገር ለመገንባት መሥራት አለብን – ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

መጋቢት 5/2014 (ዋልታ) ያማረ ቢሮ ብቻ ሳይሆን ያማረች አገር ለመገንባት መሥራት አለብን ሲሉ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ፕሬዝዳንቱ ፓርቲው ዛሬ ባስመረቀው ዋና ጽሕፈት ቤት ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ህንጻውን የሚመጥን ሥራ መስራት አለብን፤ አገር በዘይትና በስኳር የተነሳ ችግር ውስጥ እያለች ለመፍትሄው መስራት ካልቻልን አስቸጋሪ ነው ብለዋል።

በቢሯችን ልክ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የምንሠራ ሊሆን ይገባል ሲሉም መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ዛሬ የተመረቀው የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት ግንባታው በሐምሌ ወር 2009 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በአጠቃላይ 895 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጓበታልም ነው የተባለው።