ደቡብ አፍሪካ የኬኒያ ዜጎች ያለ ቪዛ ወደ ሀገሯ እንዲገቡ ፈቀደች

ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ

ኅዳር 1/2015 (ዋልታ) ከታኅሣሥ ወር ጀምሮ ኬኒያዊያን ያለምንም ቪዛ ወደ ደቡብ አፍሪካ መግባት እንደሚችሉ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ገለጹ፡፡

በኬኒያ በጉብኝት ላይ የሚገኙት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ሁለቱ አገራት የነፃ ቪዛ ጉዞን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በነበረው ስምምነት የደቡብ አፍሪካ ዜጎች ወደ ኬኒያ ያለቪዛ የሚገቡ ሲሆን ህጉ ግን በተመሳሳይ ለኬኒያ ዜጎች ተፈፃሚ ሳይሆን ቀርቷል፡፡

በነፃ ቪዛ ወደ ደቡብ አፍሪካ የገቡ ዜጎች ለ90 ቀናት በሀገሪቱ መቆየት እንደሚችሉም ተጠቁሟል፡፡

አዲሱ ተመራጭ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሁለቱ አገራት የንግድ ግንኙት ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸው የሀገሪቱ የንግድ ሚኒስትር በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለይተው እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ መስጠታቸውን የአልጄዚራ ዘገባ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW