ግንቦት 3/2013(ዋልታ) – የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት መስተዳድር ምክር ቤት 5ኛ ዙር የ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ በአማራ ክልል በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የከተሞች ደረጃ ሽግግር የሚካሄድበትን የተሻሻለውን ደንብ ላይ ዛሬ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡
በዚህም መሰረት በክልሉ ከተማ ልማት እና ቤቶች ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተሞች የፈርጅ መወሰኛ መስፈርትን አሟልተው የቀረቡትን የደብረ ብርሀን፣ የደብረ ማርቆስ እና የኮምቦልቻ ከተሞችን ወደ ሪጂዮፖሊታን ከተማ የደረጃ ሽግግር እንዲያደርጉ መወሰኑን ከአማራ ኮሚዉኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡