ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ነገ በ39 የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች ያስመርቃል

                                           የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት በ39 የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች እንደሚያስመርቅ አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአጠቃላይ 2‚518 ተማሪዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን፣ ከእዚህም 1ሺህ 8ቱ ሴቶች መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ብርሀኑ ለዋልታ ተናግረዋል።

በመጀመሪያ ዲግሪ መርኃግብር 1‚905 ተማሪዎች የሚመረቁ ሲሆን፣ በኤክስቴንሽን መርኃግብር ደግሞ 581 ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅም አቶ ዳዊት ገልጸዋል፡፡

32 ተማሪዎች ደግሞ በሁለተኛ ዲግሪ እንደሚመረቁ ተጠቁሟል።

(በሱራፌል መንግስቴ)