ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጎርፍ ለተጎዱ የጌዲኦ ዞን ነዋሪዎች ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 8/2014 (ዋልታ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች 250 ሺሕ 500 ብር የሚገመት የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ዩኒቨርሲቲው በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌና ኮቾሬ ወረዳ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተፈጠረው የጎርፍ አደጋ ለተፈናቀሉ ወገኖች ነው ድጋፍን ያደረገው።
ድጋፉ ለተቸገሩ ህፃናት እና አረጋዊያን የሚውል የዕለት ምግብን እንዳካተተ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው ላደረገው ድጋፍ የጌዴኦ ዞን አደጋ ስጋት ሥራ አመራር እና የአደጋው ሰለባዎች ምስጋና አቅርበዋል፤ መረጃው የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ነው።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!