ዲያስፓራዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአፋር ካሳጊታ ግንባር ተገኝተው ጦሩን የመሩበትን  ቦታ ጎበኙ

ታኅሣሥ 27/2014 (ዋልታ) ዲያስፓራዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፋር ክልል በግንባር ተገኝተው ጦሩን የመሩበትንና ድል ያበሰሩበትን የካሳጊታ ቦታ ጎበኙ።

በአሸባሪው ቡድን የወደመችዋን የካሳጊታ ከተማም ትላንት አመሻሽ ላይ ተመልክተዋል።

ከተለያየ አገራት በእናት አገር ጥሪ ወደ አገር ቤት የገቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአፋርና አማራ ክልሎች በአሸባሪው ሕወሓት ቡድን የተጎዱ አካባቢዎችና ተፈናቃይ ወገኖችን እየጎበኙ ነው።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በጦር ግንባር ጦር እየመሩ ድሉን ካበሰሩባቸው ስፍራዎች አንዱ በአፋር ክልል የሚገኘውን ካሳጊታን ነው የተመለከቱት።

ዲያስፖራዎቹ ይህን ታሪካዊ ስፍራ በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ለኢዜአ ገልፀዋል።

ዲያስፖራዎች ከዚህ ቀደም የልማት እና የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችንም መመልከታቸው ይታወቃል።