ዲያስፖራዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ አገራቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋገጡ

ታኅሣሥ 28/2014 (ዋልታ) የወደ አገር ቤት ጥሪን ተቀብለው አዲስ አበባ የገቡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ አገራቸውን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ዲያስፖራዎቹ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ጋር መክረዋል።
በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሰለሞን ነጋሽ፣ በአትላንታ የኢንፎርሜሽን ሲስተም አርክቴክቸር ባለሙያ አህመድ ጀማል እና በቨርጂኒያ የመረጃ እና የመሰረተ ልማት ደህኅነነት አማካሪ ፍስሃ ደስታ አገራቸውን በዘርፉ ለማገልገል እንደሚፈጉ ተናግረዋል።
የዲጂታል አግልግሎቶች ጥራት እና ደረጃን በማስጠበቅ፣ በዲጂታል ሴኩሪቲ፣ በዲጂታል ኦዲትና በዲጂታል ኢኖቬሽን ላይ ያላችውን እውቀት ለማካፍል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በዘርፉ የተስማሩና በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎችን በማስተባበር ድጋፍ እናደርጋለን ማለታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ ዲያስፖራዎቹ አገራቸውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በመምጣታቸው አመስግነው ስለኢትዮጵያ የዲጂታል ስትራቴጂ 2025 ገለፃ አድርገውላቸዋል።