ድርጅቱ ለአብርኆት ቤተ መጽሐፍ 13 ሺሕ 445 መጻሕፍት አበረከተ

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ለአብርኆት ቤተ መጽሐፍ 13 ሺሕ 445 መጻሕፍት አበረከተ።

የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ሀብቴ መጻሕፍትን ማበርከት ትውልድን መቅረፅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተጻፉ መጻሕፍት እየተሰባሰቡ ናቸው ብለዋል፡፡

አክለውም እንደ ሚዲያ ተቋማት ሌሎች ተቋማትም የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሳንቲ ሀሰን