ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን በትግራይ በህክምና ተቋማት ላይ ዝርፊያ እየተፈጸመ መሆኑን ገለጸ

ሰኔ 24/2013 (ዋልታ) – በትግራይ ክልል በሚገኙ የህክምና ተቋማት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ዝርፍያ እየተፈጸመ መሆኑን ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከትግራይ ክልል መውጣቱን ተከትሎ እንደ አዲስ አገልግሎት እየሰጡ በሚገኙ የሕክምና ተቋማት ላይ ዝርፊያ መፈጸሙን የሀኪሞች ቡድኑ በቲውተር ገጹ አስፍሯል፡፡

የቡድኑ የድንገተኛ ህክምና ፕሮግራም ሀላፊ ማሪ ካርመን ቪኖሌዝ እንዳሉት በህክምና ተቋማቱ ላይ በደረሱ ዝርፊያዎች በክልሉ ሰዎች ለጉዳት ተዳርገዋል፣ አዳዲስ አቅርቦቶች መልሰው ተወስደዋል ነዋሪዎች ከፍተኛ ችግር ተጋርጦባቸዋል ብለዋል።

ከአንድ ሳምንት በፊት በክልሉ እርዳታ ለማድረስ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድን አባል በአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች መገደሉ ይታወሳል።