ዶክተር ሊያ ታደሰ “በጎነት ለጤናችን” መርሐ ግብርን በሰቆጣ ከተማ አስጀመሩ

ነሐሴ 16/2014 (ዋልታ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ “በጎነት ለጤናችን” በሚል የተዘጋጀው የክረምት የበጎ ፈቃድ የጤና አገልግሎት መርሐ ግብርን ዛሬ በሰቆጣ ከተማ አስጀመረዋል።

ሚኒስትሯ በሀገር አቀፍ ደረጃ በክረምቱ መርሐ ግብር የነጻ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው፤ ከፍለው መታከም ለማይችሉ 100 ሺሕ ዜጎች የጤና አገልግሎት ለመስጠት መታቀዱን ጠቅሰዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በበኩላቸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረው የክረምት የጤና አገልግሎት በክልሉ 20 ሺሕ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም በቀጣይም አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉት ዶክተር መልካሙ፤ መርሐ ግብሩ ለጤና አገልግሎት መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚኖው መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።