መስከረም 27/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት አቶ ተፈሪ ፍቅሬን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ የሾሙ ሲሆን፣ ለ4 ከፍተኛ የሃላፊነት መደቦችም በሚኒስትር ማእረግ የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፡፡
- አቶ አደም ፋራህ – በሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና አስተባባሪ
- አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌ – በሚኒስትር ማዕረግ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ
- ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) – በሚኒስትር ማዕረግ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችና የህዳሴ ግድብ ዋና ተደራዳሪና አማካሪ
- ዶ/ር ለገሰ ቱሉ – በሚኒስትር ማዕረግ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ
በተጨማሪም፡
– ዶ/ር ምህረት ደበበ – የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት፤
– አቶ ፍሰሃ ይታገሱ – የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ፤
– እንዲሁም አቶ አብዱራህማን ሩቤ – የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡