ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ጋር ተወያዩ

ነሃሴ 10/2013(ዋልታ) የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግስት/ኢጋድ/ ዋና ጸሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ጄፍሪ ፊልትማን ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዋና ጸሃፊው በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ቀጠናውን በተመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከመልዕክተኛው ጋር መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

ኢጋድ እና አሜሪካ በቀጠናው ለሰላም ፣ ለመረጋጋት እና የልማት አጋርነትን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች እና ዘዴዎች ዙሪያ መምከራቸውንም ነው የገለጹት።