ዶ/ር ጥላሁን ጎሹና አጋሮቻቸው 4 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁስን ድጋፍ አደረጉ

ታኅሣሥ 17/2014 (ዋልታ) በሰሜን ኢትዮጵያ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰውን ውድመት ተከትሎ ዶ/ር ጥላሁን ጎሹ (Mihret Medical Supply) ከአጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከነትራንስፖርታቸው 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁስንና መድኃኒቶች ወደ ኢትዮጵያ መላካቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታወቁ።
አምባሳደሩ የህክምና መሳሪያዎችን፣ የህክምና ቁሳቁስንና መድኃኒቶችን በመርከብ ወደ ኢትዮጵያ ስለላኩ እጅግ እናመሰግናለን ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።