ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ወሰነ

ሚያዚያ 13/2014 (ዋልታ) የዊክሊክ መስራቹና የአሜሪካን ጨምሮ የበርካታ ሃገራትን ሚስጥራዊ መረጃዎችን ይፋ በማውጣት የተከሰሰው ጁሊያን አሳንጅ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥ የእንግሊዝ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

የአሜሪካን እና ሌሎች ሃገራትን ጥብቅ መረጃዎች በመሰለል እና በማሰራጭት ተከሶ በለንደን እስር ቤት የቆየው አሳንጅ፤ በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዲሰጥ መወሰኑ ተገልጿል፡፡

ምንም እንኳን ፍርድ ቤቱ ይህን ውሳኔ ቢያስተላልፍም፤ ውሳኔው ለእንግሊዝ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ፕሪቲ ፓታል ቀርቦ መጽደቅ ይኖርበታልም ተብሏል፡፡

ተከሳሹ ጁሊያን አሳንጅ ይግባኝ የመጠየቅ መብት እንዳለው ፍርድ ቤቱ ማሳወቁን የዘ ጋርዲያን ዘገባ አመላክቷል፡፡