ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ከጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 29/2013 (ዋልታ) – የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ከጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ሁለቱም አገሮች የነበራቸውን ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በአለም ዓቀፍ ሰላም ማስከበር ላይ የበለጠ እንደሚሰሩ ተነጋግረዋል፡፡
የመከላከያ ውጭ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄነራል ቡልቲ ታደሰ እንደገለፁት፣ ሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸው የቆየ የጋራ ትብብር ስላላቸው፣ በተለይም በሰላም ማስከበር ግዳጅ እና በቴክኖሎጂ ላይ በጋራ ይሰራሉ ብለዋል፡፡
ጄኔራሉ አክለውም በህግ ማስከበር ዘመቻው ላይ እና በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ እንደሚሰጡም ተናግረዋል ሲል የመከላከያ ሚንስቴር አስታውቋል፡፡