ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ አዲስ አበባ ገባች

ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ

ታኅሣሥ 27/2014 (ዋልታ) የሽብር ቡድኑን ትሕነግና የአጋሮቹን ወንጀል ለዓለም በማጋለጥና በመሟገት የምትታወቀው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አረጋዊ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገባች።

ጋዜጠኛዋ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዐቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ አቀባበል አድርገውላታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ለ1 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጅ ዲያስፖራዎች ያቀረበውን የወደ አገር ቤት ግቡ ጥሪ ተከትሎ ነው ጋዜጠኛ ሄርሜላ አዲስ አበባ የገባችው።

የሲቢኤስ ጋዜጠኛና ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሄርሜላ ከኢትዮጵያ አጀንዳነት ተሻግሮ ዓለም ዐቀፍ ንቅናቄ የሆነውን እምቢ ለባርነት ወይም የበቃ #Nomore እንቅስቃሴን በማስጀመርም ትታወቃለች።

በሰለሞን በየነ