ጋዜጠኛ ደረጀ ኃብተወልድ በአፋር ግምባር በመገኘት ለፀጥታ ኃይሎች ድጋፍ አደረገ

ጋዜጠኛ ደረጀ ኃብተወልድ

ኅዳር 13/2014 (ዋልታ) ጋዜጠኛ ደረጀ ኃብተወልድ በአፋር ግምባር በመገኘት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን የተረከቡት የአፋር ክልል ኮማንድ ፖስት አባል ሁሴን ሀሰን አሸባሪውን ሕወሓት ለመደምሰስ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው፣ የሚደረገው ድጋፍ እንደሚያበረታቸው ተናግረዋል፡፡

ጁንታው በሚነዛው የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሕዝቡ ሳይሸበር አካባቢውን እንዲጠብቅና ድጋፍን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል።

በቅርቡ አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ የሃገር ሰላም ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በላይ አንድነትና መተባበር እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል።

በሳራ ስዩም