ግብረ ኃይሉ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ምርመራ ዙሪያ 3ኛውን ስብሰባ እያደረገ ነው

ሐምሌ 6/2014 (ዋልታ) የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል በሰሜን ኢትዮጵያ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶች ምርመራ ዙሪያ ሦስተኛ ስብሰባውን በማድረግ ላይ ነው።

በትግራይ፣ አማራና አፋር ክልሎች የተፈፀሙ የሰብኣዊ መብት ጥሰቶችን ለመመርመር እና ለተፈፀሙ ጥፋቶች የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚኒስትሮች ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

ግብረ ኃይሉ ዛሬ እያደረገ ባለው ሦስተኛው ስብስባ የግብረ ኃይሉ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ታደሰ ካሳ (ዶ/ር) የግብረ ኃይሉ የደረሰበትን ደረጃ ሪፖርት እያቀረቡ ነው።

የነበሩ የሥራ እንቅስቃሴዎችና ተግዳሮቶች ዝርዝር ሪፖርትና በዓለም አቀፉ ሰብኣዊ መብትና በኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ጥምር የምርመራ ቡድን ምክረ ሀሳብ መሰረት የሽግግር ፍትሕ ማረጋገጥን በተመለከተ የተዘጋጀው ሰነድ ላይ ግብረ ኃይሉ በመወያየት ላይ ነው።

በዚህም የሚኒስትሮች የጋራ ግብረ ኃይል በጦርነቱ የተፈጸሙ የሰብኣዊ መብቶች ጥሰቶች እና ተጎጂዎችን መልሶ የማቋቋም ገቢራዊነት ላይ የደረሰበትን ደረጃ እየገመገመ እንደሆነ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW