ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚኒስቴሮች ስኬታማ እየሆኑ ነው አሉ

ታኅሣሥ 27/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚኒስቴሮች ያስቀመጡትን ዒላማ በማሳካት በኩል ውጤታማ እድገት አሳይተዋል አሉ።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ጉባ ወረዳ የተቋማቱን የ100 ቀናት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ አስመልክቶ በቲውተር ገጻቸው የጻፉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተገኙ መልካም ውጤቶችን የበለጠ ማሳደግና ከፈተና ውስጥ ዕድል መፍጠርን በአቅጣጫነት መቀመጡን አሳውቀዋል።