ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶዶላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዶዶላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት በክልሉ በትምህርታቸው የተሻለ አቅም ያላቸው ተማሪዎች ተለይተው የሚማሩባቸውን 7 ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች እያስገነባ ይገኛል።
ክልሉ የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እና ኢፋቦሩ በተሰኘ መርሃ ግብር የሚገነባቸው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ የሚጠቀሱ ናቸው።
ይህ ተሞክሮ ከክልል አልፎ አገራዊ እንዲሆን በማሰብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ጨምሮ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ እና የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እንዲሁም የሁለቱ ከተሞች አስተዳደሮች የተሳተፉበት ጉብኝት ተደርጓል።
አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ በተያዘው ወር መጨረሻ ተማሪዎችን ተቀብለው የመማር ማስተማር ሥራውን ይጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል።
በሚልኪያስ አዱኛ