ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

ሰኔ 12/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እየተጎበኙ ይገኛሉ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት የተጀመሩት የአንድ ወር ከ 20 ቀናት ሰው ተኮር የተቀናጀ የልማት ሥራዎች የሚከናወኑበት ሞዴል ክፍለ ከተሞችን የመፍጠር ፕሮጀክት በአምስት ክፍለ ከተሞች እየተከናወነ ይገኛል፡፡
በዛሬው እለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴና የካቢኔ አባላት በተገኙበት በቂርቆስና ልደታ ክፍለ ከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን እየጎበኙ ይገኛሉ፡፡