ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጅግጅጋ ገቡ

ጥር 17/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከከፍተኛ ልዑካን ቡድናቸው ጋር ሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ገቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጅግጅጋ ሲደርሱ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ልዑካን ቡድኑ በክልሉ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በመጎብኘት የሰብዓዊ ድጋፍ ክንውኖችን ይገመግማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።