ጠ/ሚ/ር አብደላ ሃምዶክ ከእስር ተፈቱ

ጥቅምት 17/2014 (ዋልታ) የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እና ባለቤታቸው መፈታታቸው ተገለፀ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከእስር የተፈቱት በአገሪቱ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግሥት የተለያዩ አገራት እና ኅብረቶች ካወገዙት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከጎተጎቱ በኋላ ነው ሲል ፍራንስ 24 አስነብቧል።
የሱዳን የሽግግር ሉኣላዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሌተናንት ጀነራል አብዱል ፋታህ አልቡርሀን በትላንትናው እለት በሰጡት መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለደኅንነታቸው ሲባል መታሰራቸውን ገልፀው ነገሮች ሲረጋጉ እንደሚፈቱ ተናግረው ነበር።
አልቡርሃን ፥ “ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ እኔ ቤት ነው ያሉት” ያሉ ሲሆን “ይህ የሆነው ለደኅንነታቸው ሲባል ነው” ማለታቸው የሚታወስ ነው።
መፈንቅለ መንግሥት ያደረገው ወታደራዊ ኃይሉ እስከ ሐምሌ 2015 የሲቪሉን አስተዳደር ሥልጣን ቀምቶ ለመቆየት የወሰነ ሲሆን በ10 ሺሕዎች የሚቆጠሩ ሱዳናዊያን ሥልጣን ለሲቪል አስተዳደር እንዲመለስ በመጠየቅ ተቃውሟቸው ቀጥለዋል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!