ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደብዳቤ

መስከረም 7/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዐቢይ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግልፅ ደብዳቤ ጻፉ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በጻፉት 3 ገጽ ደብዳቤ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ በዝርዝር አስፍረዋል።
ደብዳቤው የሽብር ቡድኑ ሕወሓት በአፋርና አማራ ያፈናቀላቸው ንፁሃን ዜጎች በከፋ ችግር ውስጥ ወድቀው እንደሚገኙና ቡድኑ ቤተሰቦቻቸውን በግፍ እንደገደለና የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጨምሮ ንብረት እንዳወደመ በመግለፅ ይጀምራል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ሕወሓት በትግራይ የሚገኙ ልጆቻችንን ጦርነት ውስጥ ማግዶ በሚገኝበት ወቅት የተጻፈ ግልፅ ደብዳቤ ነውም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አክለዋል።
በኢትዮጵያ ላይ እየደረሱ ያሉ የውጭ ጫናዎች ተገቢ አለመሆናቸውንም በደብዳቤያቸው አስታውቀዋል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!