ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ስለአገልጋይነት

አገልጋይነት

ጳጉሜ 02/2013 (ዋልታ) አገልጋይነት የሁላችንም ባህልና ሥነ ምግባር ከሆነ የትኛውም መስሪያ ቤት መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ የሚከበረውን የአገልጋይነት ቀን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት “አገልጋይነት ታላቅነት ነው፤ ክብር የሚገኘው ከማገልገል ነው። ፈጣሪን፣ ሀገርን፣ ሕዝብን፣ ከማገልገል ውጭ ምን ሕይወት አለ። ሁላችንም በአንድ ቦታ አገልጋዮች በሌላም ቦታ ተገልጋዮች ነን።” ብለዋል።

ሆኖም የሆኑ አካላት ብቻ እንዲያገለግሉን ከጠበቅን አገልጋይነት በአንዳንድ ቦታዎች ተፈልጎ የሚገኝ ብርቅ ሀብት ይሆንብናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቂና ብቁ አገልጋዮች የሌሏት ሀገር፣ በዕድገት መራቅና መምጠቅ ይቸግራታልም ሲሉ አክለዋል።