ጠ/ሚ/ር ዐቢይ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ የሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል ቀብሪበያን ጎበኙ

                                                                ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጥር 17/2014 (ዋልታ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመራ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ከክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በርካታ ማኅበረሰቦች መካከል አንዱ የሚገኝበትን ቀብሪበያን ጎበኙ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በጊዜያዊነት የውኃ አቅራቢ ተሽከርካሪዎችን፣ የምግብ፣ የእንስሳት መኖ እና እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መድኃኒቶችን አቅርቦት እናሳድጋለን ሲሉ አስታውቀዋል።

ድርቅ እንዳይከሰት በዘላቂነት ለመከላከል በቆላማ አካባቢዎች የውኃ ክምችትና አጠቃቀምን ለማሻሻል የጀመርናቸውን የአነስተኛ ግድቦች ግንባታ ፕሮጀክቶች እናፋጥናለን ሲሉም አክለዋል።