ጠ/ሚ/ር ዐቢይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻን መርቀው ከፈቱ

የካቲት 6/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያስገነባውን አዲስ ህንጻ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፈቱ።

በምረቃት መርሃ ግብሩ ላይ የተለያዩ ሚኒስትሮች ፣ የባንኩ የስራ ሃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው።

ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ድምቀት የሆነው 209 ሜትር ርዝመት ያለው በ165 ሺሕ ሜትር ካሬ ቦታ ላይ ያረፈው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ባንኩ የደረሰበትን ከፍታ እንደሚያሳይም ተገልጿል።

ሰማይ ጠቀሱ ህንጻ ከመሬት በታች ያሉትን ጨምሮ 55 ወለሎች እንዳሉት ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከምስረታው ጀምሮ ለህብረተሰቡ የባንክ አገልግሎትን በማዳረስ፣ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት ቴክኖሎጂዎችን በማስተዋወቅ፣ በሀገራችን የሚከናወኑ በርካታ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችን በመደገፍ እና ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት 80 ወርቃማ ዓመታትን ማሳለፉም ተገልጿል።