ጠ/ሚ ዐቢይን ጨምሮ አራት ኢትዮጵያውያን ከ100 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ ተካተቱ

በፈረንጆቹ 2020 የአፍሪካ 100 ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ዝርዝር ኒው አፍሪካ መጽሔት ይፋ አድርጓል።

መጽሔቱ ይፋ ካደረገው የ2020 የአፍሪካ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም እና በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የሚንቀሳቀሰው የንግድና የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አድማሱ ታደሰ ተካተዋል።

በመሪዎች ዘርፍ በቀዳሚነት የተቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት ተወዳጅ ከነበሩ ስሞች መከካል አንዱ ነበሩ ብሏል መጽሔቱ።

የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸነፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያደረጓትን የተለያዩ ብሄሮች እና ሀይማኖቶች አንድ ለማድረግ የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራትን አከናውነዋል ብለዋል።

በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በአፍሪካ በኢኮኖሚው እና በፀጥታው ዘርፍ የወሳኝነት ሚና ያላት የኢትዮጵያ መሪ መሆናቸውም ተገልጿል።