ጠ/ሚ ዐቢይ ሀረር ገቡ

ነሐሴ 7/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሀረር ከተማ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀረር ከተማ ሲገቡ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀረር ከተማ የተገኙት በሀረሪ ክልል በሚደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር መዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመገኘት ነው።

ተስፋዬ ኃይሉ (ከሀረር)