ጠ/ሚ ዐቢይ በፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በዓለ ሲመት ለመታደም ሞቃዲሾ ገቡ

ሰኔ 2/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም ሶማሊያ ሞቃዲሾ ገቡ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተመራው የልዑካን ቡድን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ይገኙበታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሶማሊያ ቆይታቸው በፕሬዝደንት ሀሰን ሼህ ማህሙድ በዓለ ሲመት ላይ ንግግር እንደሚያርጉም ይጠበቃል።

እንደኤፍቢሲ ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ ማህሙድ ጋር እና በበዓለ ሲመቱ ከሚታደሙ ከሌሎች የሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትሽ ምክክር ያደርጋሉም ነው የተባለው።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW