ጠ/ሚ ዐቢይ በህዳሴ ግድብ የመረጃ ልውውጥ ላይ ትኩረት ባደረገ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ

ሰኔ 18/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መረጃ ልውውጥ ላይ ትኩረቱን ባደረገ ስብሰባ ላይ ተሳተፉ፡፡

በበይነ መረብ የተካሄደው ይህው  ስብሰባ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀ መንበር ፌሊክስ ሺሴኬዲ የተዘጋጀ ሲሆን በህዳሴ ግድብ ላይ መረጃ መለዋወጥን አላማው ያደረገ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቲውተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ እንዳሉት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው ውይይት ጊዜውን የጠበቀ መሆኑን ጠቁመው ለቀጣይነቱ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።