ጠ/ሚ ዐቢይ በቻይናው ፕሬዝዳንት በተዘጋጀ ዓለም ዐቀፍ የልማት ውይይት ላይ ተሳተፉ

ሰኔ 17/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በተዘጋጀው የብሪክስ ፕላስ የከፍተኛ አመራሮች ዓለም ዐቀፍ የልማት ውይይት ላይ ተሳተፉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደነዚህ ያሉት መድረኮች የጋራ ትግበራ ሲታከልባቸው፣ እንደ ዓለም ዐቀፍ ማኅበረሰብ የተጋፈጥናቸውን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ለመፍታት ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ ብለዋል።