ጠ/ሚ ዐቢይ በኡጋንዳና በሩዋንዳ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማጠናቀቅ አዲስ አበባ ገቡ

ነሀሴ 24/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኡጋንዳ እና በሩዋንዳ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማጠናቀቅ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ  በሩዋንዳ ከፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ጋር በነበራቸው ቆይታ በጋራ ጠቀሜታ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።

በተመሳሳይም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኡጋንዳ ቆይታቸውም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን  የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።