ጠ/ሚ ዐቢይ በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል የተፈረመውን ሥምምነት አደነቁ

ጠ/ሚ ዐቢይ

መጋቢት 26/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል የተፈረመውን የሠላም ሥምምነት አደነቁ።

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች መሪዎች በወታደራዊ አቅርቦት ላይ ሳይስማሙ ያቆዩትን ጉዳይ እልባት ሰጥተው ዛሬ የሠላም ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባወጡት መግለጫ ስምምነቱን አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ሁልጊዜ ከደቡብ ሱዳን ጎን እንደምትቆም ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እና ልማት ለማምጣት የሚደረግ ጥረት መደገፏን እንደምትቀጥልም አስታውቀዋል።

የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ መሪዎች በወታደራዊ አቅርቦት ላይ ሳይስማሙ ያቆዩትን ጉዳይ እልባት ሰጥተው ስምምነት የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቱንም በጎረቤት ሱዳን የተካሄደውን ሽምግልና ተከትሎ መሆኑ ተዘግቧል።

ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር እና ተቀናቃኛቸው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የተቀናጀ ወታደራዊ ዕዝ ለመመሥረት ነው የተስማሙት፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!