ጠ/ሚ ዐቢይ በ4ኛው የአረንጎዴ አሻራ መርኃ ግብር 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ገለጹ

ሰኔ 12/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ4ኛው የአረንጎዴ አሻራ መርኃ ግብር 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ገለጹ፡፡
4ኛው የአረንጎዴ አሻራ መርኃ ግብር ሰኔ 14/2014 በይፋ ይጀመራል፡፡
ይህን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ባስተላለፉት መልእክት በ4ኛው የአረንጎዴ አሻራ መርኃ ግብር 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል የታቀደ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ለዚህም 7 ነጥብ 2 ቢሊየን ችግኝ ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ በአራት ዓመቱ የአሬንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የታቀደው 20 ቢሊየን ችግኞች የመትከል ግብ እንደሚሳካም ጠቁመዋል።
 
በአጠቃላይ በአራት ዓመቱ የአሬንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የታቀደው 20 ቢሊየን ችግኞች የመትከል ግብ እንደሚሳካም ጠቁመዋል።