መጋቢት 11/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የወንጪ ደንዲ ገበታ ለሀገር ፕሮጄክት በይፋ አስጀመሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የወንጪ ደንዲ ፕሮጄክት የአከባቢውን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚቀይር መሆኑን ገልጸው፣ ፕሮጄክቱ በታለመለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የአከባቢው ህብረተሰብ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲወጣ ጠይቀዋል።
በፕሮጄክቱ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራልና የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
(በአሳየናቸው ክፍሌ)