ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የቢላሉል ሐበሽን ማዕከል ጎብኙ

ግንቦት 05/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ጥንታዊ እስላማዊ ቅርሶች መገኛ የሆነውን ቢላሉል ሐበሺ የማህበረሰብ ሙዚየምን ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡
ማዕከሉ የኢትዮጵያውያንን ችግሮች ለመፍታት፣ ድኾችን ለመርዳትና ዕውቀትን ለማስፋፋት የሚያደርገው ጥረት አድንቀዋል።
በተለይም የረዥም ዘመናት ታሪክ ያለውን የኢትዮጵያን እስልምና ቅርሶች ለማሰባሰብና ለትውልዱ ለማሳየት የተመሠረተው ሙዝየም በከተማችን ሊጎበኙ ከሚገባቸው ቦታዎች አንዱ ነው ሲሉም ገልፀዋል።
ተቋሙ ከዚህ የበለጠ ነገር ለኢትዮጵያ እንደሚሠራም እምነቴ ነው ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።