ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ለቀድሞ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትላቸው ምስጋና አቀረቡ

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ጥር 15/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ምስጋናቸውን አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ለቀድሞ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን አረዳ ለሀገር ላደረጉት አገልግሎት እናመሰግናለን ብለዋል፡፡ በቀጣይም መልካም እድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት ባካሄደው 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባ በምትካቸው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትን ሹመት ማጽደቁ ይታወሳል፡፡