ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

መጋቢት 09/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለታንዛኒያ ሕዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጆን ማጉፉሊ ሌሊቱን ለህልፈት መዳረጋቸውን የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡