ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በገላን ከተማ የሚገኘውን የሆራ ኢንዱስትሪ ጎበኙ


ታኅሣሥ 26/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ታምርት ሁለተኛው ጉብኝታቸው በገላን ከተማ የሚገኘውን የሆራ ኢንዱስትሪ ተመልክተዋል።

በዚህ ኢንዱስትሪ ዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያ፣ መቁያ እና ሲሚንቶ ማሸጊያ ማምረቻ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢንዱስትሪ ማሳዳግ ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ትልቅ ሚና እንዳለው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ላይ ባለሀብቶች እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።