ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በጽ/ቤታቸው የሚከናወነውን የጓሮ ግብርና ተመለከቱ

ሚያዝያ 19/2014 (ዋልታ) ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት ጋር የተደረገውን ውይይት ተከትሎ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የስብሰባው ተሳታፊዎች በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ የሚከናወነውን የጓሮ ግብርና ተመልክተዋል።

የጓሮ ግብርናው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስጀመሩት የከተማ ግብርና እንቅስቃሴ አንድ አካል መሆኑ ታውቋል፡፡

የጓሮ ግብርና የሚካሄድባቸው ስፍራዎች የእንስሳት መኖ እና የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለናሙና የሚመረትባቸው መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የጓሮው ግብርናው ውሃን ያለብክነት መጠቀም መቻልን፣ ቁሳቁሶችን እንደገና በጥቅም ላይ ማዋልን እና የቦታ እጥረትን ባማከለ ሁኔታ ግብርናን መከወን እንደሚቻል በማሳየት የከተማ ነዋሪዎች የከተማ ግብርናን እንዲተገብሩ የሚያበረታታ ተግባር መሆኑ እንደተገለጸ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡