ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ታከለ ኡማን የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርገው ሾሙ

ታከለ ኡማ

ሐምሌ 9/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታከለ ኡማ በንቲ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ዋና ስራ እፈፃሚ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህም መሠረት ታከለ ኡማ ከሐምሌ 9 ጀምሮ የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር አ.ማ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል።