ጠ/ሚ ዐቢይ እያንዳንዱ ዜጋ 100 ችግኞችን እንዲተክል ጥሪ አቀረቡ

ሰኔ 14/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ4ኛው ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር እያንዳንዱ ዜጋ 100 ችግኞችን እንዲተክል ጥሪ አቀረቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ለመጪው ትውልድ እንዲሆኑ በዚህ ዙር ልተክል ካቀድኳቸው 100 ችግኞች መካከል ዐሥሩን ዛሬ ጠዋት ተክያለሁ” ብለዋል፡፡

ሁሉም ዜጋ 100 ችግኞች በመትከል ዘመቻውን እንዲቀላቀል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስፍረዋል፡፡

ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ “አሻራችን ለልጆቻችን” በሚል መሪ ሀሳብ በሚተገበረው አረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር 6 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል እቅድ ተይዞ እስካሁን ከ7 ነጥብ 6 ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን የግብርና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል።