ጠ/ሚ ዐቢይ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ጋር ተወያዩ

የካቲት 29/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ሰብኣዊ እርዳታ ተደራሽነት ዙሪያ እንዲሁም በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳይ መወያየታቸውን ከተባበሩት መንግሥታት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡